የኢትዮጵያ የምርት ገበያ በ2018 በጀት ዓመት የ48.83 ቢሊዮን ብር ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ
19:19 03.09.2026 (የተሻሻለ: 19:24 03.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የምርት ገበያ በ2018 በጀት ዓመት የ48.83 ቢሊዮን ብር ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ
ምርት ገበያው የግብርና እና የወጪ ንግድ ምርቶችን በማገበያየት የዓመታዊ ዕቅዱን 167.8% እንዳሳካ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።
ቁልፍ አሃዞች፦
◻ በበጀት ዓመቱ 29.1 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የወጪ ምርቶችን ለመገበያየት አቅዶ ከእቅዱ በላይ 48.83 ቢሊዮን ብር ማሳካት ችሏል።
◻ አፈፃፀሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ21.63 ቢሊዮን ብር ወይም የ79% ብልጫ አሳይቷል።
◻ በ12 ወራት ውስጥ ለ14,327 የምርት ናሙናዎች (8,499 የቡና እንዲሁም 5,828 የቅባት እህሎችና ጥራጥሬዎች) የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሰጥቷል።
ተቋሙ የግብይት አድማሱን ለማስፋት ኦፓል፣ ጥጥ፣ ቆዳ እና የቆዳ ወጤት ምርቶችን ወደ ግብይት ስርዓቱ ለማስገባት የሚያስችል የጥራት ደረጃ ውል ዝግጅት አጠናቋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X