ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ በተ.መ.ድ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ መደረጉን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ በተ
ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ በተ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ በተ.መ.ድ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ መደረጉን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ

 

ይህ የተገለጸው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባለብዙ ወገን የሰብዓዊ መብቶች ትብብር ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ግሪጎሪ ሉኪያንስቴቭ በፕሪቶሪያ ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ዲፓርትመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዞሊሳ ማብሆንጎ ጋር ነሐሴ 27 ካደረጉት ምክክር በኋላ ነው።

"ዋናው ትኩረት በዓለም አቀፍ መድረኮች፤ በዋናነት በተ.መ.ድ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር ላይ ነበር። የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች የፖለቲካ መጠቀሚያ መደረጋቸውን እንዲሁም ለጂኦፖለቲካዊ ጫና እና ኢ-ፍሐሃዊ ውድድር መሣሪያነት ማገልገላቸውን እንዴት መከላከል እንደሚቻል በዝርዝር ተወያይተናል" ሲሉ ሉኪያንስቴቭ ገልጸዋል።

በምክክሩ ላይ የተሳተፉት አካላት ገለልተኝነትን ማስጠበቅ፣ የተ.መ.ድ ቻርተርን ማክበር እና በሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ የሚስተዋለውን ድርብ መስፈርት መዋጋት አስፈላጊነት ላይ ተስማምተዋል።

"የዓለም አቀፍ ተቋማትን ገለልተኝነት መጠበቅ፣ የተ.መ.ድን ቻርተር በጥብቅ መከተል እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በሚገመግሙበት ወቅት ድርብ መስፈርት አሠራርን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል" ሲሉ ዲፕሎማቱ ተናግረዋል።

ሉኪያንስቴቭ እና ማብሆንጎ በዘረኝነት ላይ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ 25ኛ ዓመትን አስመልክተው፤ ሁሉንም ዓይነት የዘር አድልዎ መዋጋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ሁለቱ ወገኖች በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠልም ተስማምተዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0