አልጄሪያ በሀገሪቱ ከተከሰተው አጥፊ የሰደድ እሳት ጋር ተያይዞ ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞት ቅጣትን ዳግም ስራ ላይ ልታውል ነው

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ በሀገሪቱ ከተከሰተው አጥፊ የሰደድ እሳት ጋር ተያይዞ ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞት ቅጣትን ዳግም ስራ ላይ ልታውል ነው

በፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ተቡን የተመራው የአልጄሪያ ከፍተኛ የደህንነት ምክር ቤት፤ ሆን ብለው የደን እሳት በሚለኩሱ ወንጀለኞች ላይ የሞት ቅጣት እንደገና እንዲጣል ጥሪ አቅርቧል።

ፕሬዚዳንት ተቡን በሀገሪቱ ማዕከላዊ እና ምሥራቃዊ ክልሎች ከተከሰተው ተከታታይ የሰደድ እሳት አደጋ በኋላ እሳት በሚለኩሱ አካላት ላይ የሞት ቅጣትን በማካተት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እስከ ጳጉሜን 5 ድረስ እንዲሻሻል ለፍትሕ ሚኒስቴሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

ℹ አልጄሪያ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ የሞት ቅጣትን በተግባር አግዳ ቆይታለች። ቅጣቱ ሕግ ውስጥ ለተለያዩ ወንጀሎች ቢካተትም፤ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ምንም ዓይነት የሞት ቅጣት አልተፈጸመም።

የሞት ቅጣት በአፍሪካ፦

ለሁሉም ወንጀሎች ያገዱ፦ ወደ 26 የሚጠጉ ሀገራት፣

ለመደበኛ ወንጀሎች ያገዱ፦ ሦስት ሀገራት (ቡርኪና ፋሶ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋና) እንደ ሀገር ክህደት ወይም የጦር ወንጀል ላሉ ልዩ ጥፋቶች ብቻ አስቀርተውታል፣

የዕገዳ ውሳኔ ያሳለፉ፦ ወደ 17 የሚጠጉ ሀገራት በሕግ ወይም በተግባር የሞት ቅጣትን አግደዋል፣

በሕግ የያዙ እና የሚተገብሩ፦ ቀሪዎቹ ሀገራት በሕጋቸው ያስቀሩት ሲሆን የሞት ቅጣቱ በስፋት የሚፈጸመው ደግሞ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ግብፅን ጨምሮ በጥቂት ሀገራት ውስጥ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0