የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሕፃናትን የቆዳ በሽታዎች የሚለይ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥርዓት አለማ
17:21 03.09.2026 (የተሻሻለ: 18:34 03.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሕፃናትን የቆዳ በሽታዎች የሚለይ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥርዓት አለማ
ኢንስቲትዩቱ በሰው ሠራሽ አስተውሎት አማካይነት በዋናነት የሕፃናትን ቆዳ የሚያጠቁ ሦስት የሕመም ዓይነቶችን በትክክል መለየት የሚያስችል ውጤታማ ቴክኖሎጂ ማልማቱን አስታውቋል።
የተለዩት የቆዳ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው?
'አቶፒክ ደርማታይተስ' (ቆዳን የሚያደርቅና የሚያሳክክ)፣
'ፓፑላር አርቲካሪያ' (በነፍሳት ንክሻ የሚፈጠር አለርጂ)፣
'ስካቢስ' (እከክ - በቆዳ ንክኪ የሚተላለፍ)።
ሥርዓቱ ቀጥታ ከሐኪሞች የተገኘውን ልምድና እውቀት ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሞዴሎች በማስተማር የዳበረ እና የቴክኖሎጂው ትክክለኛነት በበቂ ሁኔታ ተፈትሾ መረጋገጡን አሃዱ ሬዲዮ ዘግቧል።
🟧 ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የዕውቅና ሰርተፊኬት አግኝቷል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X