የማሊ መከላከያ ሠራዊት በኦፕሬሽን ዱጉኮሎኮ የሽብር ቡድኖችን የሎጂስቲክስ ማዕከል ደበደበ
16:03 03.09.2026 (የተሻሻለ: 16:04 03.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማሊ መከላከያ ሠራዊት በኦፕሬሽን ዱጉኮሎኮ የሽብር ቡድኖችን የሎጂስቲክስ ማዕከል ደበደበ
የማሊ የጦር ኃይሎች በቲምቡክቱ በሚገኘው የሞዲያኮይ ቀጣና የታጣቂዎችን የሎጂስቲክ ማዕከል እንደመቱ የማሊ ሠራዊት ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ውጊያው የተቀሰቀሰው ወታደሮች ረቡዕ በአካባቢው አስር ያህል ግለሰቦች የጦር መሣሪያዎች እና የተሽከርካሪ ጎማዎችን ለማንሳት ሲዘጋጁ ከተመለከቱ በኋላ ነው።
ጥቃቱ በሚያዝያ 2025 የተጀመረው ሀገር አቀፍ ዘመቻ 'ኦፕሬሽን ዱጉኮሎኮ' አካል ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓላማዎች ሰንቋል፦
▪ በማሊ አጠቃላይ ግዛት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፤
▪ የሽብርተኝነት እና የወንጀል ሥጋቶችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ፣
▪ የዜጎችን ነፃ እንቅስቃሴ ማረጋገጥ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X