የዓረብ ሊግ ኃላፊ የሱዳናውያንን የሀገራዊ ውይይት ተነሳሽነት ጥረት ደገፉ

© telegram sputnik_ethiopiaየዓረብ ሊግ ኃላፊ የሱዳናውያንን የሀገራዊ ውይይት ተነሳሽነት ጥረት ደገፉ
የዓረብ ሊግ ኃላፊ የሱዳናውያንን የሀገራዊ ውይይት ተነሳሽነት ጥረት ደገፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2026
ሰብስክራይብ

የዓረብ ሊግ ኃላፊ የሱዳናውያንን የሀገራዊ ውይይት ተነሳሽነት ጥረት ደገፉ

ናቢል ፋህሚ በሱዳን ብሔራዊ አካላት የሚመራውንና ከፖለቲካ፣ ከሲቪል እና ከማኅበረሰብ ቡድኖች ጋር ሁሉን አቀፍ የምክክር መድረክ ለመፍጠር ያለመውን ተነሳሽነት በደስታ ተቀብለዋል።

ቁልፍ ነጥቦች፦

ዋና ፀሐፊው የሉዓላዊነት ምክር ቤቱ በሕግ የተጣሉ ገደቦችን በማንሳት፤ ለተሳታፊዎች ያለመከሰስ መብት ለመስጠት መወሰኑን የደገፉ ሲሆን እርምጃው ሂደቱ በራሳቸው በሱዳናውያን ባለቤትነት እንዲመራ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

ፋህሚ ሁሉም የሱዳን ፖለቲካዊ እና ሲቪል ኃይላት በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በችግሩ እና በሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያሉ ልዩነቶች ሀገራዊ ውይይት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የትኛውም ዘላቂ መፍትሔ በሱዳናውያን መመራት እንዳለበት የገለጹት ኃላፊው፤ የዓረብ ሊግ ሚና ሀገራዊ ጥረቶችን መደገፍ እንጂ መተካት እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0