ኢትዮ ቴሌኮም 605 የሞባይል ጣቢያዎች በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ሊገነባ ነው
ኢትዮ ቴሌኮም 605 የሞባይል ጣቢያዎች በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ሊገነባ ነው
ይህ የተገለጸው ተቋሙ ኔክስት ሆራይዘን የተሰኘውን የሦስት ዓመት ስትራቴጂ የ2018 በጀት ዓመት ትግበራ እና የቀጣይ ዓመት እቅድ ባሳወቀበት መድረክ ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኔክስት ሆራይዘን ስትራቴጂ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ማሳካት ዓላማው ያደረገ እንደሆነ በመድረኩ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።
እስከ 2020 ዓ.ም በሚቆየው ስትራቴጂ የታቀዱ ሥራዎች፦
የሞባይል ጣቢያዎችን ወደ 13,238 ማድረስ፣
የአራተኛ ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎትን 97% ማድረስ፣
የ5ኛ ትውልድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር ወደ 100 ማሳደግ፣
የክላውድ መሠረተ ልማቶችን እና የዳታ ማዕከላትን ማስፋፋት።
ዋና ሥራ አስኪያጇ የስትራቴጂው የመጀመሪያ ዓመት ትግበራ በስኬት መጠናቀቁን ጠቁመዋል።
የተመዘገቡ ስኬቶች፦
የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች 96.2 ሚሊዮን ደርሷል፣
60 ሚሊየን ዜጎች የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፣
18 ቢሊየን የሚሆን ብድር ለደንበኞች ተሰራጭቷል።
በ2019 በጀት ዓመት 1 ሺህ 628 ተጨማሪ የሞባይል ጣቢያዎች እንደሚገነቡ እና ከነዚህ ውስጥ 605ቱ በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚከናወኑ ይፋ አድርገዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X