ኔቶ 'ሰው ሠራሽ ህልውናውን' ለማራዘም ሰበቦችን እያፈላለገ ይገኛል — ላቭሮቭ

ሰብስክራይብ

ኔቶ 'ሰው ሠራሽ ህልውናውን' ለማራዘም ሰበቦችን እያፈላለገ ይገኛል — ላቭሮቭ

ኔቶ ወደ እስያ በመስፋፋት፤ ህልውናውን ለማቆየት አዳዲስ ምክንያቶችን እየፈለገ እንደሆነ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቭላዲቮስቶክ በተካሄደው የምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ተናግረዋል።

 

የላቭሮቭ ተጨማሪ ንግግሮች፦

ጥምረቱ ከሶቪየት ኅብረት ውድቀት በኋላ ከዋርሶ ስምምነት ጋር አብሮ መፍረስ ሲገባው፤ በምትኩ አዳዲስ ተልዕኮዎችን መፈለጉን ቀጥሏል።

የኔቶ የአፍጋኒስታን ዘመቻ "በአስከፊ ሁኔታ ከተጠናቀቀና" ኃይሎቹ ከሸሹ በኋላ፤ ጥምረቱ የሶቪየትን ስጋት የፈጠራ ውጤት በሆነው "የሩሲያ ስጋት" ተክቶታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የኢንዶ-ፓሲፊክ ስምምነት ድርጅት ለመመስረት እያጤነ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ኔቶ በእስያ መሠረተ ልማቱን ለመዘርጋት እየሞከረ ይገኛል።

እንዲህ ያሉ ዕቅዶች በእስያ-ፓሲፊክ ቀጣና ውስጥ "የኔቶን ርዕዮተ ዓለም" እና "የኔቶን አስተሳሰብ" መልሰው እንደሚፈጥሩ ላቭሮቭ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0