ግብፅ እና ቻይና በመገበያያቸው የሚያደርጉትን የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ

© telegram sputnik_ethiopiaግብፅ እና ቻይና በየሀገራቱ የገንዘብ መገበያያ የንግድ ልውውጣቸውን ለማሳደግ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ
ግብፅ እና ቻይና በየሀገራቱ የገንዘብ መገበያያ የንግድ ልውውጣቸውን ለማሳደግ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2026
ሰብስክራይብ
ግብፅ እና ቻይና በመገበያያቸው የሚያደርጉትን የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ ተስማሙ - የጋራ መግለጫ

ስምምነቱ የተደረሰው የሁለቱን ሀገራት 70ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ምክንያት በማድረግ የቻይና ፕሬዚዳንት በግብፅ ባደረጉት መንግሥታዊ ጉብኝት ወቅት ነው።

ሌሎች የውይይቱ ዋና ዋና ውጤቶች፦

የመቀነት እና መንገድ ትብብር፡ ግብፅን በኢንዱስትሪ፣ ሎጂስቲክ፣ ታዳሽ ኃይል እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቀጣናዊ ማዕከል ለማድረግ በማለም፤ በግብፅ የ2030 ራዕይ እና በቻይና የመቀነት እና መንገድ ተነሳሽነት መካከል ጥልቅ ትስስር መፍጠር፣

ዋና ዋና ፕሮጀክቶች፡ በመሠረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ኢነርጂ፣ ጠፈር፣ ቴክኖሎጂ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ትብብር ማድረግ፣

የንግድ ሚዛን፡ የግብፅ ምርቶች ወደ ቻይና ገበያ በስፋት እንዲገቡ ማድረግ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራትን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ለማድረግ በሚያስችለው የቀዳሚ ተጠቃሚነት ስምምነት ላይ ምክክር ማካሄድ፣

ፖለቲካዊ ቅንጅት፡ በፍልስጤም የሁለት ሀገር መፍትሄን መደገፍ፣ የማፈናቀል ዕቅዶችን ውድቅ ማድረግ እና በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረብ፣

ቀይ ባሕር እና ሱዳን፡ የቀይ ባሕር አስተዳደር በባሕሩ አዋሳኝ ሀገራት እንዲመራ መደገፍ እና በሱዳን ያለውን ጦርነት አሳታፊ በሆነ የፖለቲካ ሂደት ለማስቆም ቁርጠኝነት ማሳየት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0