- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከድምፅ እስከ ታሪክ፡ የግሎባል ደቡብ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው የቋንቋ ገመድ

ከድምፅ እስከ ታሪክ፡ የግሎባል ደቡብ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው የቋንቋ ገመድ
ሰብስክራይብ
ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ14 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ በቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያን ባህልና ቋንቋ በቀጥታ ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ፈጥሯል።
“ይህማ[ቋንቋ] በጣም ትልቅና የላቀ ሚና አለው። ቋንቋ በሁለት ሕዝቦችና በሁለት አገሮች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቻይናውያን አማርኛን ሲማሩም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የንግድ፣ የልማትና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በቀጥታ ለመረዳት ያስችላቸዋል” ሲሉ በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ(ዶ/ር) ናቸው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0