- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

በርሊን ኮንፈረንስ፡ የምዕራባውያን ኢ-ፍትሐዊነት እና በደል በአፍካውያን ላይ

በርሊን ኮንፈረንስ፡ የምዕራባውያን ኢ-ፍትሐዊነት እና በደል በአፍካውያን ላይ
ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን ሸማቾች እንዲሆኑ፣ ከዛ በፊት አይተው የማያውቁትን የአውሮፓ እቃ መሸመት፣ መጠቀም እንዲችሉ ብዙ ተዘዋዋሪ መንገዶችን ይጠቀማሉ። አፍሪካውያን ያለነዛ ሽቀጦች ህይወታቸውን መምራት እንዳይችሉ አድርገው አጣብቂኝ ውስጥ ይከቷቸዋል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ከዶ/ር ደቻሳ አበበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት በክፍል አንድ፣ የአውሮፓ ወራሪ ኃይሎች በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት አፍሪካን የመቀራመት ስምምነት በአፍሪካ እና አፍሪካውያን ላይ ስላንጸባረቁት ኢ-ፍትሐዊነት እና ስላደረሱት በደል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ከዶ/ር ደቻሳ አበበ ጋር በመሆን እንዳስሳለን፡፡
በክፍል ሁለት፡ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ዓለም አቀፍ ሽግግር እንዲሁም ሩሲያ በ2026 የተባበሩት መንግስታት የዋና ፀሃፊ ምርጫ ውስጥ ያላትን ሚና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የ3ኛ ድግሪ እጩው ከሆኑት ሀዋቂ በቀለ ጋር ተወያተንበታል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
አዳዲስ ዜናዎች
0