ኢትዮጵያ አዳዲስ የጤና ስጋቶችን ለመግታት የድንበር ተሻጋሪ የጤና ክትትልዋን አጠናከረች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ አዳዲስ የጤና ስጋቶችን ለመግታት የድንበር ተሻጋሪ የጤና ክትትልዋን አጠናከረች
ኢትዮጵያ አዳዲስ የጤና ስጋቶችን ለመግታት የድንበር ተሻጋሪ የጤና ክትትልዋን አጠናከረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.09.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ አዳዲስ የጤና ስጋቶችን ለመግታት የድንበር ተሻጋሪ የጤና ክትትልዋን አጠናከረች

ሀገሪቱ ከድንበር ድንበር ተላላፊ ህመሞችን ለመከላከል ከአጎራባች ሀገራት ጋር የመግባቢ ስምምነቶችን እየተፈራረመች እንደሆነ የኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

 

ዝግጁነቱን ለማጠናከር በየሦስት ወሩ የተግባር ልምምዶችን እያካሄደ እንደሚገኝ ኢንስቲትዩቱ ጨምሮ ገልጿል።

 

ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው የየብስ መተላለፊያዎች የተባሉት፦

 

ሞያሌ፣

ጋምቤላ፣

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣

መተማ።

 

በኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ማዕከል አስተባባሪ ኤቢሴ አበሰ፤ "በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የዕለት ተዕለት ቅኝት በማድረግ፤ ያገኟቸውንም መረጃዎች ለማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ሪፖርት እያደረጉ ነው" ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0