የአዲስ አበባ ከንቲባ መዲናዋ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደረጃዋን የጠበቀች የጤና ቱሪዝም መዳረሻ እንደምትሆን አረጋገጡ

© telegram sputnik_ethiopiaየአዲስ አበባ ከንቲባ መዲናዋ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደረጃዋን የጠበቀች የጤና ቱሪዝም መዳረሻ እንደምትሆን አረጋገጡ
የአዲስ አበባ ከንቲባ መዲናዋ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደረጃዋን የጠበቀች የጤና ቱሪዝም መዳረሻ እንደምትሆን አረጋገጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.09.2026
ሰብስክራይብ

የአዲስ አበባ ከንቲባ መዲናዋ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደረጃዋን የጠበቀች የጤና ቱሪዝም መዳረሻ እንደምትሆን አረጋገጡ

 

ዕቅዱን እውን ለማድረግ የመንግሥት እና የግል የጤና ተቋማት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና መስጠት የሚችሉበትን አቅም መገንባት እንዳለባቸው፤ ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ በከተማ አስተዳደሩ የቀጣይ 5 ዓመታት ዕቅድ ዙሪያ በተካሄደ ውይይት ላይ ተናግረዋል።

 

ግቡን ለማሳካት እሳካሁን የተሠሩ ሥራዎች፦

 

▪ ባለፉት ዓመታት ዘጠኝ አዳዲስ ዘመናዊ ጤና ጣቢያዎች ወደ አገልግሎት ገብተዋል፣

▪ ቀደም ሲል የጤና ተቋም ያልነበራቸውን አምስት ወረዳዎች ጤና ጣቢያዎች አግኝተዋል፣

▪ በ40 ነባር የጤና ጣቢያዎች ላይ ሰፊ የማስፋፊያና የማጠናከሪያ ሥራ ተከናውኗል፣

▪ ዘውዲቱ መታሰቢያ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና ዳግማዊ ምኒሊክን ጨምሮ ነባር ሆስፒታሎች ታድሰዋል፣

▪ ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ ግዙፍ ሆስፒታሎች ተከፍተዋል።

 

ግቡ ኢትዮጵያውያን ወደ ውጭ ሀገር ሳይሄዱ በሀገራቸው ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል እውን የሚያደርግ ነውም ተብሏል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0