ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ለመቁረጥ አሲራለች - የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopiaግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ለመቁረጥ አሲራለች - የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር
ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ለመቁረጥ አሲራለች - የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.09.2026
ሰብስክራይብ

ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር ለመቁረጥ አሲራለች - የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ፤ ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ክፍተቶች እና ተቃዋሚ ኃይሎች በመጠቀም ሀገሪቱን ለማዳከም አሁንም እየሠራች እንደሆነ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

 

ኢትዮጵያ የዓባይ ምንጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የግብጽ ባለሥልጣናት እና ሽርኮቻቸው ሀገሪቱን ለማዳከም እና ከቀይ ባሕር እንድትርቅ ለማድረግ ሸርበዋል ሲሉ ተናግረዋል።

 

ኢትዮጵያ ኤርትራ ከመገንጠሏ በፊት በታሪክ ምፅዋን እና ዓሰብን ማስተዳደሯን እንዲሁም የባሕር ኃይል እንደነበራትም አስታውሰዋል።

 

“ኢትዮጵያ ከባሕር በር ተቆርጣ ልትቀር አትችልም” ያሉት አምባሳደር ሽፈራው፤ ለዚህም የሀገሪቱን የሕዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ፣ እየጨመረ የመጣውን የገቢና ወጪ ንግድ፣ ለቀይ ባሕር ቅርብ መሆኗን እና ከአካባቢው ወደቦች ጋር ያላትን ታሪካዊ ትስስር በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0