የሲኤፍኤ ፍራንክ መገበያያ ሳይሆን የፈረንሳይ መንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ነው - ካሜሩናዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
11:06 02.09.2026 (የተሻሻለ: 11:14 02.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሲኤፍኤ ፍራንክ መገበያያ ሳይሆን የፈረንሳይ መንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ነው - ካሜሩናዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
ሁሉም የሲኤፍኤ ፍራንክ ክፍያዎች በቀጥታ ወደ ዩሮ የሚቀየሩ በመሆኑ ፈረንሳይ ከሂደቱ ኮሚሽን እንድትሰበስብ አስችሏታል ሲሉ ያም ንቲምባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህም ከዚህ አሠራር መራቅ መጀመር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የፓን-አፍሪካ የክፍያ ስርዓት የብሔራዊ ገንዘቦች ዝውውርን ቢፈቅድም ችግሩን አይፈታውም ሲሉም ባለሙያው አፅንኦት ሰጥተዋል።
ስርዓቱ የተፈጠረው በውጭ የበላይነት ዐውድ በመሆኑ የኒዮኮሎኒያሊዝም ስርዓት መርሆች እና ማዕቀፎችን ያንፀባርቃል ሲሉ ንቲምባ ገልጸዋል።
ይህንን ሁኔታ ለመቅረፍ ሙሉ በሙሉ የተለየ አቀራረብ ያስፈልጋል ያሉት ባለሙያው፤ የምዕራብ አፍሪካ ቀጣናን በማዋሃድ የአፍሪካ ሀገራትን ማስፋፋት የሚል ሃሳብ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X