- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የባህል ወረራ - ሌላኛው ቅኝ-ግዛት፣ የሆሊውድ ፊልሞች በአፍሪካዊነት ስነ-ልቦና ላይ በማሳደር ላይ ያሉት ተጽዕኖ

የባህል ወረራ - ሌላኛው ቅኝ-ግዛት፣ የሆሊውድ ፊልሞች በአፍሪካዊነት ስነ-ልቦና ላይ በማሳደር ላይ ያሉት ተጽዕኖ
ሰብስክራይብ
“የሆሊውድ ተጽእኖ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፤ ጉዳቱ ያመዝናል ግን ቢሆንም ጠቃሚነቱም ደግሞ የሚካድ አይደለም። [...] ምዕራባውያን በአብዛኛው ፊልሞቻቸው ላይ የበላይነታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ […] በተቃራኒው ደግሞ የአፍሪካን ኋላቀርነት እና አስከፊ ገጽታ ለመገንባት ይሞክራሉ፤ ይህም ትውልዱ ራሱን እና ሀገሩን የሚያይበትን መንገድ የተበላሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡” ሲል አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ፣ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ግጭት ጉዳዮች ተመራማሪ እና መምህር አሌክሳንደር ኃይማኖት(ዶ/ር) አፍሪካ ከጥሬ እቃ አቅራቢነት እሴትን ወደ መጨመር እንዴት ልትሸጋገር እንደምትችል ሀሳባቸውን የሚያጋሩን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የፊልም እና ቲያትር ባለሙያ ከሆነው ከአርቲስት ቢኒያም ወርቁ ጋር በመሆን የምእራብያውያን የፊልም እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ቀሪውን ዓለም የሚቃኙበት እና የሚያቀርቡበት መንገድ እንዴት ባለ መልኩ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንዳለ፣ አፍሪካ እና አፍሪካውያን ስለእራሳቸው ስላላቸው አመለካከት ላይ በተለይ የሆሊውድ የፊልም ኢንደስትሪ ያደረሰው አሉታዊ ጫና እንዲሁም የአፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የስነጥበብ ባለሙያዎች ይህን የባህል ወረራ እንዴት ባለ መልኩ መመከት እንደሚችሉ በሰፊው ቃኝተነዋል፡፡
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0