በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 1.25 ሚሊዮን ቶን ማዕድን የማቀናበር አቅም ያለው ፋብሪካ ሊገነባ ነው
18:30 01.09.2026 (የተሻሻለ: 18:34 01.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 1.25 ሚሊዮን ቶን ማዕድን የማቀናበር አቅም ያለው ፋብሪካ ሊገነባ ነው
የፋብሪካው አስገንቢ ሚድሮክ ጎልድ፤ የግንባታ መሣሪያዎች እንዲያቀርብለት ከኦስትሪያው የሲሚንቶ እና ማዕድን ኩባንያ ሴምቴክ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።
ሴምቴክ፤ በስምምነቱ መሠረት በዓመት 1 ሚሊዮን 250 ሺህ ቶን ወርቅ አዘል ድንጋይ ማቀነባበር የሚችል የወርቅ ፋብሪካ ማሽነሪ የማምረትና የመገንባት ተግባር እንደሚያከናውን ሚድሮክ ጎልድ አስታውቋል።
ሚድሮክ በመተከል ዞን 33,000 ኪሎ ግራም የሚገመት ትልቅ የወርቅ ክምችት ማግኘቱን በነሐሴ 2006 ዓ.ም አስታውቆ እንደነበር የሀገር ውስጥ ሚዲያ በዘገባው አስታውሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X