የቢሽኬክ መግለጫ ከአፍሪካ ጥቅም አኳያ የትኞቹን ጉዳዮች አካቷል?

ሰብስክራይብ

የቢሽኬክ መግለጫ ከአፍሪካ ጥቅም አኳያ የትኞቹን ጉዳዮች አካቷል?

በሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ የጸደቀው ሰነድ፤ የድርጅቱን ዕድገት እና ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች በተመለከተ የአባል ሀገራቱን የጋራ አቋም አውጥቷል።

ለአፍሪካ አኀጉር አግባብነት ያላቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

አባል ሀገራቱ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

ዓላማ፦ የሰላማዊ ግጭት አፈታት ፖሊሲን በመከተል እና ከግጭት በመራቅ፤ ሁሉም ሀገራት በውሳኔ አሰጣጥ እና በጥቅም ክፍፍል ላይ እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማረጋገጥ።

አባል ሀገራቱ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም አቀፍ የመልሶ ግንባታና ልማት ባንክ ባሉ ተቋማት ውስጥ የታዳጊ ሀገራትን የልማት ውክልና እና ሚና ለማሳደግ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ መዋቅር እንዲሻሻል ተሟግተዋል።

ዓላማ፦ የኤስ.ሲ.ኦ የልማት ባንክ፣ የልማት ፈንድን እና የኤስ.ሲ.ኦ የኢንቨስትመንት ፈንድን ጨምሮ የድርጅቱን የውስጥ የፋይናንስ ዘዴዎች መዘርጋት።

የኤስ.ሲ.ኦን የልማት ባንክ ለማቋቋም የሚደረገውን ሂደት ገምግመዋል።

ውጤት፦ አሠራራቸው እና መስፈርቶቻቸው በአፍሪካ ሀገራት ዘንድ ብዙ ጊዜ ከሚነቀፉት፤ እንደ አይኤምኤፍ/ዓለም ባንክ ካሉ የተለመዱ ተቋማት ውጭ አፍሪካ ለፕሮጀክቶቿ አማራጭ ወይም ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጭ የምታገኝበትን መንገድ ይከፍታል።

አዲስ "የኤስሲኦ አጋር" ምድብ ይፋ ተደርጓል።

ውጤት፦ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ሌሎችንም ከድርጅቱ ፕሮጀክቶች ጋር በተደራጀ እና በተዋቀረ ሁኔታ ማጣመር ያስችላል።

ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦

ዓለም አቀፍ ደህንነት እና ግጭቶች

የኤስሲኦ አባላት፤ አንዳንድ ሀገራት የራሳቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ሌሎችን የሚጎዱበት አካሄድ ተቀባይነት እነደሌለው ገልጸዋል።

የኢራን ሁኔታ

ተሳታፊዎቹ በመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ጥልቅ ስጋታቸውን ገልጸው፤ ለኢራን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ያላቸውን ድጋፍ አረጋግጠዋል እንዲሁም ችግሩ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

የባሊስቲክ ሚሳኤል መከላከያ ሥርዓቶች 

እነዚህን ሥርዓቶች በሀገራት ወይም በተለያዩ ጥምረቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለገደብ ማስፋፋት የዓለም አቀፍ ደህንነት እና መረጋጋትን ያናጋል ብለዋል።

ጠፈር

ተሳታፊዎቹ በጠፈር ላይ የሚደረገውን የጦር መሣሪያ ውድድር መከላከል እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተውበታል፤ ጠፈር ከጦር መሣሪያ ነፃ ሆኖ ለሰላማዊ ዓላማዎች ብቻ እንዲውል ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0