በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ስርዓት ትግበራ ከሀገር በቀል ዕውቀት ጋር አልተጣጣመም - ኢትዮጵያዊ ፀሐፊ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ስርዓት ትግበራ ከሀገር በቀል ዕውቀት ጋር አልተጣጣመም - ኢትዮጵያዊ ፀሐፊ

ዘመናዊ ትምህርት ወይም አስኳላን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የኢትዮጵያን እሴት፣ ባሕል፣ ቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ እንዳይዳብር የማድረግ ስውር ሴራ በምዕራባውያን ተደርጓል ሲሉ ባለቅኔ፣ ገጣሚና ፀሃፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ይህች ሀገር በራሷ ባሕል፣ በራሷ ቋንቋ፣ በራሷ ሥነ-ጽሁፍ፣ በራሷ ፊደል እየዳበረች ከመጣች፤ ዓድዋ ላይ የጀመረችውን ድል በኪነ-ጥበብ

መስክም ታካሂዳለች ብለው ነው የሚያስቡት። የሚያስቡትም፣ እየሠሩ ያሉትም ይሄው ነው። እና ስለዚህ እሷን ለማደናቀፍ የሚችል ምን እንፍጠር ሲባል አስኳላን በኢትዮጵያ ውስጥ ማስገባት የግድ ነበረ" ሲሉ አብራርተዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0