የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ጠባሳዎችን ለማከም የካሳ ክፍያ ተገቢ ነው - ተመድ (UN)

© telegram sputnik_ethiopiaየአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ጠባሳዎችን ለማከም የካሳ ክፍያ ተገቢ ነው - ተመድ (UN)
የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ጠባሳዎችን ለማከም የካሳ ክፍያ ተገቢ ነው - ተመድ (UN) - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.09.2026
ሰብስክራይብ

የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ጠባሳዎችን ለማከም የካሳ ክፍያ ተገቢ ነው - ተመድ (UN)

​"ሰውን እንደ ንብረት የሚቆጥረውን የባሪያ ስርዓት ለማስቀጠል የተፈጠረው የፀረ-ጥቁር ዘረኝነት፤ የባሪያ ንግድ ከተወገደ በኋላም ለረጅም ጊዜ ቆይቶ ይገኛል" ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር መድልዎ አስወጋጅ ኮሚቴ ባወጣው አዲስ አጠቃላይ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ገልጿል።

በኮሚቴው የቀረቡ ዋና ዋና የውሳኔ ሃሳቦች፦

​🟠 የካሳ እርምጃዎች የገንዘብ እና ከገንዘብ ውጪ የሆኑ እርምጃዎችን ያጣመሩ መሆን ይገባቸዋል። መብትን መመለስ፣ የገንዘብ ካሳ፣ መልሶ ማቋቋም፣ የአዕምሮ ካሳ እና ድርጊቱ ዳግም ላለመፈጸሙ ዋስትና መስጠትን ያካተቱ መሆን አለባቸው።

​🟠 ሀገራት ዘረኝነት እና የዘር ተዋረድን የሚያስቀጥሉ ወይም የካሳ ፍትሕን የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥ ሕጎችን እና ፖሊሲዎችን መሻር ወይም ማሻሻል አለባቸው።

​🟠 ሀገራት የካሳ እርምጃዎችን በመቅረጽ እና በመተግበር ሂደት ላይ የትውልደ አፍሪካውያን እና የተጎጂ ማኀበረሰቦችን ሙሉ ተሳትፎ ማረጋገጥ አለባቸው።

​🟠 ከባሪያ ንግድ ትርፍ ያገኙ የግል ተቋማት—የሐይማኖት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ባንኮች እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ጨምሮ—ለካሳ ፍትሕ አስተዋፅዖ ማድረግ አለባቸው።

​🟠 ሀገራት ስለ ታሪካዊ በደሎች ትክክለኛ ትምህርት መሰጠቱን ማረጋገጥ እንዲሁም የተሳሳቱ መረጃዎችን እና የዘር የበላይነት ርዕዮተ ዓለሞችን መዋጋት አለባቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0