የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጮች በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምላሾች ውስጥ ድርሻቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጮች በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምላሾች ውስጥ ድርሻቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጮች በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምላሾች ውስጥ ድርሻቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.08.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጮች በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምላሾች ውስጥ ድርሻቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ

‍ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ቀውሶችን በተመለከተ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት መድረኮች በሚሰጧቸው ምላሾች የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጮችን በበቂ ሁኔታ እንደማይጠቀሙ አዲስ ጥናት አረጋግጧል።

ጥናቱ ምን አመላከተ?

⤵ በቻትጂፒቲ ትንተና ከተካተቱት 81 የመረጃ ምንጮች መካከል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምንጮች ድርሻ 4.9 በመቶ (4 ያህል ብቻ) ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ምላሾች ውስጥ 68.8 በመቶ የመረጃ ምንጮች ከተባበሩት መንግሥታት እና ከባለብዙ ወገን ተቋማት የተወሰዱ ናቸው።

ዩኒሴፍ፣ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ እና ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በግንባር ቀደምነት ከፍተኛውን የመረጃ ድርሻ ይዘዋል።

ጥናቱ በጄሚኒ፣ ዲፕሲክ፣ ቻትጂፒቲ እና ፐርፕሌክሲቲ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መድረኮች ላይ የተካሄደ ነው።

ℹ የሀገር ውስጥ ተቋማት መረጃዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ አለመልቀቅ፣ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት በቀላሉ የሚፈለጉ ሜታዳታዎችን አለመጠቀም እና የመረጃ አስተዳደር ክፍተቶች ለክፍተቱ መነሻ መሆናቸው ተጠቅሷል ሲል የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0