ኢትዮጵያ አኅጉር በቀል የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ለሰላምና ደህንነት ሥራዎች በኃላፊነት ጥቅም ላይ እንዲውል ድጋፏን ገለፀች
14:52 31.08.2026 (የተሻሻለ: 15:04 31.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ አኅጉር በቀል የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ለሰላምና ደህንነት ሥራዎች በኃላፊነት ጥቅም ላይ እንዲውል ድጋፏን ገለፀች
ኢትዮጵያ ከነሐሴ 14 እስከ 24፣ 2018 ዓ.ም ሲካሄድ በቆየው 26ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት እና የ21ኛው አኅጉራዊ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባዎች ውጤታማ ተሳትፎ እንዳደረገች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአኅጉራዊ ስብሰባው በኢትዮጵያ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (የአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የዲጂታል ጤና ቻምፒዮን) መሪነት አፍሪካ በቀል ሰው ሠራሽ አስተውህሎት ለግጭት ትንተና፣ ለተቋማዊ ዝግጅት እና ለወቅታዊ ውሳኔዎች እንዲውል ኢትዮጵያ ድጋፏን ገልጻለች።
በአፍሪካ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን ማጠናከር እና ውሳኔዎችን በፍጥነት ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባ ተሰምሮበታል።
🪙 ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት የምታደርገውን የበጀት አስተዋፅኦ ከደረጃ 2 ወደ ደረጃ 1 በማሳደግ አኅጉራዊ ሰላምን በራስ አቅም ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
"በአፍሪካ ችግሩ የሕግና የተቋማት እጥረት ሳይሆን የውሳኔዎችና የቅድመ-ማስጠንቀቂያዎችን በፍጥነት ወደ ተግባር አለመቀየር ነው፤ ይህንን ክፍተት በቴክኖሎጂና በራስ አቅም መሙላት አለብን" ስትል አሳስባለች።
ጉባኤው በአፍሪካ የግጭት መከላከልና መፍትሔ መስጫ ዘዴዎችን የማጠናከር ዓላማ ያነገበውን የሉዋንዳ የድርጊት መርኃ-ግብር አፅድቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X