ፑቲን ለዓመታዊው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ቢሽኬክ ገቡ
14:32 31.08.2026 (የተሻሻለ: 14:34 31.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን ለዓመታዊው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ቢሽኬክ ገቡ
የሩሲያ ፕሬዚዳንት በቢሽኬክ ማናስ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፤ ብሔራዊ ምግቦች፣ ዘፈኖች እና ውዝዋዜዎችን ጨምሮ በባሕላዊ የኪርጊዝ እንግዳ ተቀባይነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አስሩም የድርጅቱ አባል ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን እና የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያንን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት መሪዎች በኪርጊዝስታን ዋና ከተማ ይሰበሰባሉ።
ቭላድሚር ፑቲን በጉባኤው ዋና ዋና ኩነቶች ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ከውጭ ሀገራት መሪዎች ጋር ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችንም ያደርጋሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X