🪖 7,000 የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ወታደሮች የዩክሬን ጦርን እየደገፉ ይገኛሉ - ጥናት

© telegram sputnik_ethiopia🪖 7,000 የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ወታደሮች የዩክሬን ጦርን እየደገፉ ይገኛሉ - ጥናት
🪖 7,000 የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ወታደሮች የዩክሬን ጦርን እየደገፉ ይገኛሉ - ጥናት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.08.2026
ሰብስክራይብ

🪖 7,000 የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ወታደሮች የዩክሬን ጦርን እየደገፉ ይገኛሉ - ጥናት

በአሁኑ ወቅት ከ70 ገደማ ሀገራት የተወጣጡ ቅጥር ወታደሮች በዩክሬን ጦር ውስጥ እየተዋጉ እንደሚገኙ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የምስራቅ ጥናቶች ኢንስቲትዩት የሳይንሳዊ እና ትንተና መረጃ ማዕከል ኃላፊ ኒኮላይ ፕሎትኒኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ያካሄደውን ጥናት ጠቅሰው ፕሎትኒኮቭ እንደተናገሩት፤ "እነዚህ ወታደሮች የጸረ-ሩሲያ አቋም ከሚያንፀባርቁ የ70 ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ከአውሮፓ እና ከላቲን አሜሪካ የመጡ ናቸው።"

አክለውም ኮሎምቢያውያን ትልቁን ቁጥር እንደሚይዙና ከእነሱም በተጨማሪ እንደ ሜክሲኮ፣ ብራዚል እና ሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት ዜጎች ይገኙበታል።

ከአውሮፓውያኑ መካከል ፖላንዶች እና ፊንላንዶች በብዛት የሚገኙ ሲሆን፣ በአንጻሩ ከአሜሪካ እና ከጆርጂያ የመጡ የውጭ ቅጥረኛ ወታደሮች ቁጥር አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ጠቁመዋል።

ወደ ዩክሬን የተጓዙ ቅጥረኛ ወታደሮች በሰጧቸው በርካታ ቃለ-መጠይቆች የዩክሬን ኃይሎች የውጊያ ቅንጅት ደካማ መሆኑን እና በውጊያው ውስጥ በሕይወት የመተረፍ እድላቸው በጣም አነስተኛ መሆኑን አምነዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ዩክሬን የውጭ ሀገር ቅጥረኛ ወታደሮችን እንደ "ማገዶ" እየተጠቀመችባቸው መሆኑን እና ለሩሲያ ጦር ህጋዊ የጥቃት ኢላማ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0