የሊቢያ ተፎካካሪ ወገኖች በሁለት ዓመታት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ - የተባበሩት መንግሥታት

© telegram sputnik_ethiopiaየሊቢያ ተፎካካሪ ወገኖች በሁለት ዓመታት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ - የተባበሩት መንግሥታት
የሊቢያ ተፎካካሪ ወገኖች በሁለት ዓመታት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ - የተባበሩት መንግሥታት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.08.2026
ሰብስክራይብ
የሊቢያ ተፎካካሪ ወገኖች በሁለት ዓመታት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ - የተባበሩት መንግሥታት

ከሊቢያ አራቱ ዋና ዋና ተቋማት የተወጣጡ ሁለት ሁለት ተወካዮች የተሳተፉበት እና "4+4" በመባል በሚታወቀው የውይይት መድረክ የተደረሰውን ይህን ስምምነት፣ እሁድ ዕለት በትሪፖሊ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊቢያ ድጋፍ ተልዕኮ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመውታል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፡

🟠 ምርጫው በ24 ወራት ውስጥ በአንድ አስፈፃሚ አካል ስር እንዲካሄድ፤

🟠 በምርጫ ሕግ ማዕቀፍ ላይ ማሻሻያዎች እንዲጸድቁ፤

🟠 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የሀገር ከፍተኛ ምክር ቤት ስምምነቱን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያጸድቁት፤

🟠 እነዚህ አካላት ማጽደቅ ካልቻሉ፣ ወገኖቹ ስምምነቱን በሀገር በቀል አሰራሮች አማካኝነት እንደ ሕገ-መንግስታዊ ሰነድ ለማጽደቅ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት ምክር ቤት ድጋፍ ለማግኘት እንደሚሰሩ ተገልጿል።


በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የዋና ጸሐፊው ልዩ ተወካይ ሀና ቴቴ ፤ "የዛሬው ስምምነት በሊቢያ የምርጫ ሂደቱን አግዶ የቆየውን ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ውጥረት ለመፍታት ትልቅ እርምጃ ነው" ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0