የእሬት መድኃኒትነት እና የምርት መጠን ከሚበቅልበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት እንዳለው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ

ሰብስክራይብ

የእሬት መድኃኒትነት እና የምርት መጠን ከሚበቅልበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት እንዳለው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ

በኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በተካሄደው ጥናት፣ የእሬት ተክል የሚበቅልበት ወረዳ እና ዝርያው ተክሉ የሚኖረውን የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድናት መጠን እና የቅጠል ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚወስነው ተረጋግጧል።

ዋና ዋና መረጃዎች

🟠 የተጠኑ አካባቢዎች (3 ወረዳዎች)፦ ከአንኮበር፣ ከመርሃቤቴ እና ከከዎት የተሰበሰቡ 6 የተለያዩ የእሬት ዝርያዎች በጋራ አንድ ቦታ ተተክለው ተመዝግበዋል።

🟠የከዎት እና የአንኮበር የእሬት ዝርያዎች ከፍተኛ የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድን ስብጥር እና ከፍተኛ የቅጠል ምርት በማስመዝገብ በግንባር ቀደምነት ተለይተዋል።

🟠 ጥናቱ አርሶ አደሮች ተክሉን "ወንዴ" እና "ሴቴ" እሬት ብለው የሚለዩበትን ባህላዊ እውቀት ሳይንሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን አረጋግጧል።

🟠 ለመድኃኒት፣ ለሥነ-ውበት እና ለምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እሬትን የዝርያ ጥራቱን ተመልክቶ መግዛት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።

"በተመሳሳይ እንክብካቤ የበቀሉ የእሬት ዓይነቶች እንኳን በመጡበት ቦታ እና በዘረመል ልዩነታቸው ምክንያት የሚሰጡት የጄል (የዝልግልግ ቅባት) መጠን እና የመድኃኒትነት ኃይል የተለያየ ነው፤ ይህም ለአርሶ አደሮች እና ለፋብሪካዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይሰጣል" ሲል ዓለም አቀፉ 'ዲስከቨር ፕላንትስ' ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት አመላክቷል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0