ቦይንግ ለ32 የኬንያውያን ተጎጂ ቤተሰቦች የ11 ቢሊዮን ሽሊንግ ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተዘገበ
18:50 30.08.2026 (የተሻሻለ: 18:54 30.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቦይንግ ለ32 የኬንያውያን ተጎጂ ቤተሰቦች የ11 ቢሊዮን ሽሊንግ ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተዘገበ
መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በተከሰተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ 32 የኬንያውያን ተጎጂዎች ቤተሰቦች አጠቃላይ 11 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ (በግምት 85 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) የካሳ ክፍያ ሊፈጸምላቸው መሆኑ ተዘግቧል።
የኬንያ ሚዲያ እንደዘገበው፣ በአማካይ ለአንድ ቤተሰብ ከ300 ሚሊዮን እስከ 350 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ይደርሳቸዋል (ክፍያው እንደየተጎጂው ዕድሜ፣ ገቢ እና የቤተሰብ ጥገኝነት ይለያያል)።
ገንዘቡ በአሜሪካ የሕግ ኩባንያዎች በኩል ወደ ኬንያ ተልኮ ለሕጋዊ ወራሾች ክፍያው ይፈጸማል ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X