ቻይና እና ሩሲያ የባህር ላይ ማነቆዎችን ለማስቀረት የሚያስችል የሀገር ውስጥ የውሃ መንገድ አማራጭን እያጠኑ ነው

ቻይና እና ሩሲያ የባህር ላይ ማነቆዎችን ለማስቀረት የሚያስችል የሀገር ውስጥ የውሃ መንገድ አማራጭን እያጠኑ ነው
በዓለም ዙሪያ የሚነሱ ግጭቶች የባህላዊ የባህር ማጓጓዣ መስመሮችን ተጋላጭነት ይፋ ባደረጉበት በአሁኑ ወቅት፣ ሁለቱ ሀገራት የቻይናን ምዕራባዊ ክፍሎች ከአርክቲክ ውቅያኖስ ጋር የሚያገናኝ የወንዝ መስመር ለማልማት እያሰቡ መሆኑን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስ' ዘግቧል።
🟠 4,248 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ መስመር ከቻይና ሺንጂያንግ ግዛት ተነስቶ በካዛክስታን በኩል የሚያልፈውን የኢርቲሽ ወንዝ የሚከተል ሲሆን፣ ከሩሲያው ኦብ ወንዝ ጋር ከተቀላቀለ በኋላ ወደ አርክቲክ ውቅያኖስ ይፈሳል።
🟠 ይህ መስመር ቻይና አሁን ላይ ወደ አርክቲክ ለመግባት የምትጠቀምበትን መንገድ ችግር ይፈታል፤ የቻይና የአሁኑ መንገድ ከአሜሪካ በኩል እገዳ ቢጣልበት በቀላሉ ሊዘጋ የሚችል ጠባብ መተላለፊያ በሆነው በቤሪንግ ስትሬት ላይ የተመሰረተ ነው።
🟠 ከማላካ እና ቤሪንግ ስትሬት መተላለፊያዎች ከሚያልፉት መደበኛ የባህር መስመሮች በተለየ፣ ይህ የሀገር ውስጥ ኮሪደር ከምዕራባውያን የባህር ኃይል እገዳ እና ቅኝት ነፃ የሚሆን ሲሆን፣ ዋናው መስመር ጥቅም ላይ መዋል ባይችል እንደ አማራጭ የሚያገለግል ነው።
በአርክቲክ በኩል የሚያልፈው የሰሜን ባህር መስመር የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የበለጠ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የጂኦፖለቲካ ውጥረቶችም አዳዲስ አማራጮችን የመፈለግ ፍላጎትን አፋጥነውታል። መስመሩ ከፍተኛ የጊዜ ቁጠባ የሚያስኝ ሲሆን፣ ከቻይና ወደ አውሮፓ በአርክቲክ በኩል የሚደረግ ጉዞ 20 ቀናት ብቻ ይወስዳል፤ ይህም በስዊዝ ካናል በኩል ከሚወስደው የ40 ቀናት ጉዞ ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ቅናሽ አለው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X