የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢዎች እጥረት ችግር ወደ 16% ዝቅ ማለቱ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢዎች እጥረት ችግር ወደ 16% ዝቅ ማለቱ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ከአቅራቢዎች መዝገብ ማስፋፋትና አዳዲስ አሰራሮችን ከመተግበር ጋር ተያይዞ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ክፍተት ከነበረበት 27 በመቶ ወደ 16 በመቶ ዝቅ ማለቱን አስታውቋል።

ዋና ዋና መረጃዎች

▪ ከዚህ ቀደም የነበረው 27% የመድኃኒት አቅራቢዎች እጥረት ወደ 16% ዝቅ ብሏል፡፡

24 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የመድኃኒት ግዢ ውሎች ከ5,000 የጤና ተቋማት ጋር ተፈርመዋል፡፡

16.3 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች ለጤና ተቋማት የቀረቡ ሲሆን አፈፃፀሙ 70% ደርሷል፡፡

▪ የአቅርቦት ምንጭ ማወቅ አቅም ከሰባት ዓመታት በፊት ከነበረበት ከ50% በታች አሁን ወደ 95% አድጓል፡፡

▪የአገልግሎቱ አሰራር፣ ግዢና የመድኃኒት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሲስተም እየተመራ ይገኛል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0