ሕዝባችንን በጨለማ ውስጥ ትተን ለዳታ ማይኒንግ ተቋማት ኃይል አንለቅም - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ሰብስክራይብ
ሕዝባችንን በጨለማ ውስጥ ትተን ለዳታ ማይኒንግ ተቋማት ኃይል አንለቅም - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውሃ ግድቦች የውሃ መጠን በመቀነሱ ምክንያት ለሕዝብና ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ቅድሚያ ለመስጠት ሲባል ለዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች የሚቀርበውን የኃይል መጠን በ75 በመቶ መቀነሱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታውቋል።

ዋና ዋና መረጃዎች

ከተፈረመው ውል አንጻር የቀረበው የኃይል መጠን ወደ 23% ዝቅ ብሏል (የ75% ቅናሽ ተደርጓል)፡፡

የውሳኔው ምክንያት ወደ ግድቦች የሚገባው የውሃ መጠን ቢያንስ በ20% መቀነሱ እና የደረቃማ ወቅት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መኖሩ ነው።

ዳታ ማይኒንግ ባለፈው የበጀት ዓመት 50.37 ቢሊዮን ብር ገቢ ያስገኘ ቀዳሚ ዘርፍ ቢሆንም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል አቅርቦቱ ገታ ተደርጓል።

ሆኖም በጥቅምት ወር (ከክረምቱ ማብቂያ በኋላ) በሚደረግ የውሃ መጠን ግምገማ መሠረት አቅርቦቱ የሚሻሻል ወይም የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘው ቪዲዮ ቦሌ ሌሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ የቢትኮይን ማይኒንግ ዌስት ዳታ ማዕከልን ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0