ቬኔዙዌላ ከአሜሪካ ጋር ባደረገችው የነዳጅ ስምምነት ከሚሸጠው አንድ በርሜል ነዳጅ 19 ዶላር ታገኛለች - ሮድሪጌዝ

ሰብስክራይብ
ቬኔዙዌላ ከአሜሪካ ጋር ባደረገችው የነዳጅ ስምምነት ከሚሸጠው አንድ በርሜል ነዳጅ 19 ዶላር ታገኛለች - ሮድሪጌዝ

የቬኔዙዌላ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን የነዳጅ ስምምነት የፋይናንስ አሰራር ዝርዝር ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ ቬኔዙዌላ ተመርቶ ከሚሸጠው እያንዳንዱ በርሜል ነዳጅ 19 ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ገልጸዋል፤ ይህም በስምምነቱ ዘመን ውስጥ በድምሩ እስከ 209 ቢሊዮን ዶላር የሚያስገኝ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

የ25 ዓመታት ስምምነት፦ 17 ስትራቴጂካዊ የነዳጅ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም በቀን የሚመረተውን ነዳጅ መጠን ወደ 1.5 ሚሊዮን በርሜል ማሳደግ ነው፡፡

የባለቤትነት ክፍያ (ሮያሊቲ) መጠን፦ ቢያንስ 16% ፣ የትርፍ ግብር 34% ሲሆን ይህም በአንድ በርሜል $65 ዋጋ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ቬኔዙዌላ የምታቀርበው፦ የነዳጅ ሀብት፣ የኢንዱስትሪ መሰረት እና ከ100 ዓመታት በላይ ያከማቸችውን የዘርፉን ልምድ ታካፍላለች፡፡

አሜሪካ የምታቀርበው፦ ሀብቶችን መልሶ ለመገንባትና ለማልማት የሚያስፈልግ ካፒታል እና ቴክኖሎጂ ይሆናል፡፡

ሮድሪጌዝ በንግግራቸው፤ ቬኔዙዌላ "በተጣሉ ማዕቀቦች ምክንያት በእጅጉ የተጎዳውን" የነዳጅ ኢንዱስትሪዋን መልሳ ለመገንባት የውጭ ካፒታል እና ቴክኖሎጂን የምትጠቀም ቢሆንም፣ "በሀብቷ ላይ ያላትን ባለቤትነት እና ሉዓላዊነት እንደጠበቀች ትቀጥላለች" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0