ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ 14.4 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ አገኘች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ 14.4 ሚሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ አገኘች

ሀገሪቱ በአኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ የቅባት እህሎች እና የግብርና ምርቶችን በዋናነት ወደ አፍሪካ ሀገራት በመላክ ከ14.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገበያ ገቢ ማስገኘቷን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሰነድ ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የንግድ መጠን

የወጪ ንግድ፦ 14.4 ሚሊዮን+ ዶላር
የገቢ ንግድ ፦ 8.65 ሚሊዮን ዶላር

ዋና ዋና የወጪ ምርቶች

⭐የቅባት እህሎች እና ተዛማጅ ምርቶች፦ 5.7 ሚሊዮን ዶላር
⭐በቆሎ፦ 900,000 ዶላር ገደማ
⭐ሳሙና እና የኬሚካል ምርቶች፦ 780,000 ዶላር

የወጪ ንግድ መዳረሻዎች ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና እና አልጄሪያ ሲሆኑ ኬንያ፡ የኢትዮጵያን 93% የወጪ ንግድ (13.35 ሚሊዮን ዶላር) እና 5.61 ሚሊዮን ዶላር የገቢ ንግድ በመሸፈን ቀዳሚዋ የንግድ አጋር ሆናለች።

መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በማዕቀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ጭነቶችን ስትልክ የተደረገው የማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0