አትሌት አዲሱ ጎበና የሲድኒ ማራቶንን የውድድሩን አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ

ሰብስክራይብ
አትሌት አዲሱ ጎበና የሲድኒ ማራቶንን የውድድሩን አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ

የ24ኛው የሲድኒ ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት እና በአዲስ የውድድሩ ክብረወሰን ተጠናቋል። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር አትሌት አዲሱ ጎበና 2:04:42 በሆነ ሠዓት በመግባት በዓመቱ ዐበይት የማራቶን ውድድሮች ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ፅፏል።

ዋና ዋና መረጃዎች

ቀደም ሲል በኃይለማርያም ኪሮስ ተይዞ የነበረውን 2:06:06 በ1 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ተሻሽሏል፡፡

አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ 2:04:46 በሆነ ሠዓት 2ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።

የሴቶች ውድድር ውጤት

ኬንያውያኑ አትሌቶች ፒርስ ጅፕችርችር እና አይሪን ቼፕታይ ተከታትለው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ሹሬ ደምሴ፣ ሄቨን ሀይሉ እና መሠረት አበባየሁ በቅደም ተከተል ከሦስት እስከ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገበተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0