ሩሲያ ከማሊ ጋር በጤናው ዘርፍ የጋራ ስምምነት ለማድረግ ሀሳብ አቀረበች
16:45 29.08.2026 (የተሻሻለ: 16:54 29.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከማሊ ጋር በጤናው ዘርፍ የጋራ ስምምነት ለማድረግ ሀሳብ አቀረበች
በማሊ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ መሠረት ሀሳቡ የቀረበው የሩሲያ የጤና ምክትል ሚኒስትር ኦሌግ ሳላጋይ ከአዲስ አበባው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጎን ለጎን ከማሊ የጤና ሚኒስትር አሳ ባዲያሎ ቱሬ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
🟠 ሳላጋይ ስምምነቱ የሕክምና ምርቶች አቅርቦትና ምርት፣ የተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች ስምሪት፣ እንዲሁም ለጤና ባለሙያዎች የመጀመሪያ ደረጃና ቀጣይነት ያለው የሥልጠና ፕሮግራሞችን እንዲያካትት ሀሳብ አቅርበዋል።
🟠 የሩሲያ ወገን የስምምነቱን ትግበራ የሚያመቻች ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ሀሳብ አቅርቧል።
🟠 ማሊ በራሷ የሕክምና ምርቶችን፣ በተለይም የኩላሊት እጥበት እና የወሊድ ቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶችን በማሊ የፋርማሲዩቲካል ምርቶች ፋብሪካ አማካኝነት የማምረት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።
🟠 በተጨማሪም ሳላጋይ ሩሲያ ለማሊ የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ ባማኮ ከሞስኮ ጋር በደህንነት፣ በኢነርጂ፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የምታደርገውን ትብብር እያሰፋች ትገኛለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X