ስዋሂሊ የታንዛኒያን 'የቋንቋ ቱሪዝም' እና የዲጂታል እድገት እያፋጠነው መሆኑን ባለሙያ ገለጹ

ሰብስክራይብ

ስዋሂሊ የታንዛኒያን 'የቋንቋ ቱሪዝም' እና የዲጂታል እድገት እያፋጠነው መሆኑን ባለሙያ ገለጹ

በታንዛኒያ የብሔራዊ ስዋሂሊ ምክር ቤት የቋንቋ ባለሙያ የሆኑት ኩሳንጃ አማኑኤል ኩሳንጃ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ሰዎች ወደ ታንዛኒያ እና ምስራቅ አፍሪካ የሚያቀኑት "በተለይ ቋንቋውን እና ባህሉን ለመለማመድ" ነው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ስዋሂሊ በወጣቱ ትውልድ ዘንድ ለመማሪያነት ብቻ ሳይሆን የሥራ እና የንግድ ዕድል ሆኖ እየታየ ነው፤ ወጣት ታንዛኒያውያን ስለ አገር ውስጥ ቅርሶች እና የቱሪስት መዳረሻዎች የሚያዘጋጇቸውን የስዋሂሊ ይዘቶች በመጠቀም "በቋንቋው እና በአገሪቱ ላይ ፍላጎት እንዲፈጠር" እያደረጉ ይገኛሉ ሲሉ ጠቁመዋል።

የዲጂታል ዕድሎች እያደጉ በመጡ ቁጥር ቋንቋው በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የበለጠ የማስፋፊያ ዕድል እንዳለው ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መድረኮች ከበፊቱ የተሻለ በስዋሂሊ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት በመጀመራቸው አዎንታዊ እርምጃዎች እየታዩ ነው።

ℹ ከ200 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ሰዎች የሚነገረው ስዋሂሊ ቋንቋ በታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ይሠራበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0