ሱዳን በምዕራባውያን የሚመሩ የሰብዓዊ መብቶች ምርመራዎችን ለምን እንተገዳደረች እንደምትገኝ ባለሙያ ማብራሪያ ሰጡ

ሰብስክራይብ

ሱዳን በምዕራባውያን የሚመሩ የሰብዓዊ መብቶች ምርመራዎችን ለምን እንተገዳደረች እንደምትገኝ ባለሙያ ማብራሪያ ሰጡ

ካርቱም "ሰብዓዊ መብቶችን ዝም ብላ አልቀበልም እያለች አይደለም፤ ይልቁንም ምርመራ የማካሄድ ሥልጣን ያለው ማን ነው? በምንስ መመሪያ እና በማን ፈቃድ? የሚሉትን ነጥቦች እየተገዳደረች ነው" ሲሉ ሱዳናዊዉ ባለሙያ ዶ/ር መሐመድ ሁሴን አብደልዋሂድ መሐመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የዶ/ር መሐመድ አስተያየት የመጣው ሱዳን በቻይና የሚመራውን የ29 አገራት ጥረት ተክተላ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሐቅ አጣሪ ተልዕኮን በተመለከተ ብሪታንያ ያቀረበችውን የውሳኔ ሃሳብ ረቂቅ ለማገድ ጥሪ ባቀረበችበት ወቅት ነው።

በባለሙያው የተሰጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 በምዕራባውያን እምነት ላይ፦  ምዕራባውያን አብዛኛውን ጊዜ መንግሥት የግጭቱ አካል በሚሆንበት ወቅት የሀገር ውስጥ ምርመራዎች ተአማኒነት ሊኖራቸው አይችልም ሲሉ ክስ ያቀርባሉ። የአፍሪካ መንግሥታት ግን ይህንን ምዕራባውያን ለአፍሪካ ተቋማት እምነት እንደሌላቸው ማሳያ አድርገው ይወስዱታል፡፡

🟠 የቻይና አቋም በተመለከተ፦ ቤጂንግ ተጠያቂነት በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መርሆዎች መሠረት መከናወን አለበት፤ ለፖለቲካዊ ጣልቃገብነቶች መጠቀሚያ መሳሪያ መሆን የለበትም ስትል ትከራከራለች፡፡

🟠 የደቡባዊው ዓለም ተቃውሞን አስመልክቶ፦ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ላይ የበለጠ ተፅዕኖ ለመፍጠር እየጠየቁ ይገኛሉ። የሱዳንም ጉዳይ ከዚህ የተነጠለ አይደለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0