የኢራን ተመራማሪዎች በብርሃን አማካኝነት የካንሰር ሕዋሳትን የሚያጠፋና 80% ውጤታማ የሆነ ስማርት "ጄል" አዘጋጁ
09:01 29.08.2026 (የተሻሻለ: 09:04 29.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢራን ተመራማሪዎች በብርሃን አማካኝነት የካንሰር ሕዋሳትን የሚያጠፋና 80% ውጤታማ የሆነ ስማርት "ጄል" አዘጋጁ
ይህ "ስማርት ሃይድሮጄል" (ፈሳሽ ቅባት) የጡት ካንሰር ዕጢዎችን በጥንቃቄ ኢላማ በማድረግ ለማከም የኬሞቴራፒ እና በብርሃን ላይ የተመሠረተ ሕክምናን ያጣመረ ነው።
🟠 ጄሉ ከተፈጥሯዊና ከሰውነት ጋር ተስማሚ ከሆነ "ካይቶሳን" ከተባለ ንጥረ ነገር የተሠራ ነው፡፡
🟠 መድኃኒቱን በተቆጣጠረ ሁኔታ የሚለቅ ሲሆን፣ የሌዘር ብርሃን ሲያርፍበት ይነቃቃል፡፡
🟠 በተለየ ሁኔታ የካንሰር ሕዋሳትን የሚጎዱ የኦክሲጅን ውህዶችን ያመነጫል፡፡
🟠 የተደረጉት ሙከራዎች እንደሚያሳዩት፣ ጄሉ ጤናማ ሕዋሳትን ሳይነካ ከ80% በላይ የሚሆኑትን የጡት ካንሰር ሕዋሳት ማጥፋት ችሏል፡፡
ይህ አቀራረብ ከተለመዱት የጡት ካንሰር ሕክምናዎች በተሻለ፣ አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትል እና ቀጥተኛ ዒላማውን ብቻ የሚያጠቃ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዘጋጀ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X