- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአፍሪካ ቀንድ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም፦ የጂኦፖለቲካ የስበት ማዕከልነትና ሉዓላዊ ውሳኔ

የአፍሪካ ቀንድ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም፦ የጂኦፖለቲካ የስበት ማዕከልነትና ሉዓላዊ ውሳኔ
ሰብስክራይብ
"አፍሪካውያን የራሳቸውን ውሳኔ በራሳቸው የመወሰን ስትራቴጂካዊ ነፃነት ሊኖራቸው የሚችለው ለራሳቸው የሰላምና የልማት ጥረቶች የገንዘብ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው። በውጭ ፋይናንስ ላይ ጥገኛ ከሆንክ የሀሳብህ ባለቤት መሆን አትችልም።" ሲሉ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ምርምር ዋና ዳይሬክተር ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ የባህረ ሰላጤው ሀገራት፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እንዲሁም የምዕራባውያን ሀገራት እጃቸውን ወደ ቀይ ባህርና ኤደን ባህረ-ሰላጤ በሰፊው እያዘረጉ ባለበት በዚህ ወቅት የአፍሪካ ቀንድ የትኩረት ማዕከል መሆኗን ዳግም አረጋግጧል ።
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) የአፍሪካ ጉዳዮች ምርምር ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) ጋብዘን በእነዚህ አንኳር ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0