ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን መገንባት ልትጀምር ነው – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን መገንባት ልትጀምር ነው – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ለአዲሱ በጀት ዓመት ተጨማሪ ሁለት ወይም ሦስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር አቅደናል ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

አዲሶቹ ፕሮጀክቶች፦

የገናሌ ዳዋ 6፣ የውኃ ኃይል ማመንጫ

በደዋሌ አካባቢ የሚገኝ የነፋስ ኃይል ፕሮጀክት

በሶማሌ ክልል የሚገነባ 125 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ናቸው።

ከሰሞኑ፣ የግብጽ የውኃና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሴዊላም ኢትዮጵያ አዳዲስ ግድቦችን የመገንባት እቅዷን መንግሥታቸው እንደማይፈቅድ ከዛቱ በኋላ፣ የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ሀገራቸው የዓባይ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ እንደማትጠይቅ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የተቋማቸውን የበጀት ዓመት ክንውን እና የአዲሱ ዓመት ዕቅድ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ በመጠናቀቅ ላይ ስላሉ ፕሮጀክቶች የተናገሩበትን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0