ኢትዮጵያ የውሃ ጥራትን በማረጋገጥ የዜጎችን ጤና የሚያስጠብቅ አዲስ ላብራቶሪ ሥራ አስጀመረች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የውሃ ጥራትን በማረጋገጥ የዜጎችን ጤና የሚያስጠብቅ አዲስ ላብራቶሪ ሥራ አስጀመረች

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሀገሪቱን የውሃ ሀብት ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊ ስፔሻላይዝድ የውሃ ጥራት ላብራቶሪ እና ዘርፈ-ብዙ ህንፃዎችን መርቆ ሥራ አስጀምሯል።

የላብራቶሪው አበርክቶ፦

ንጹሕና አስተማማኝ የመጠጥ ውሃ፦ የውሃ ጥራትን በዘመናዊ የላብራቶሪ ቴክኖሎጂ በጥብቅ ለመፈተሽ ስለሚያስችል፣ ማኅበረሰቡ ከውሃ ወለድ በሽታዎች የተጠበቀና አስተማማኝ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኝ ያደርጋል።

የምግብ ደኅንነትና የምርታማነት ዕድገት፦ ለመስኖና ለግብርና የሚውል ውሃ ጥራትን በማረጋገጥ፣ ጤናማና ምርታማ የግብርና ምርት ለሕዝቡ እንዲቀርብ ያስችላል።

ማዕከሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፣ የ3-በ-1 ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያካተተ ነው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0