ከሉዓላዊነት ጥበቃ እስከ ምግብ ዋስትና፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዓሣ ሀብት ልማት
17:35 28.08.2026 (የተሻሻለ: 17:44 28.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከሉዓላዊነት ጥበቃ እስከ ምግብ ዋስትና፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዓሣ ሀብት ልማት
ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ላይ የሚገኘው አየር ኃይሉ፣ የሠራዊቱን የምግብ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የዓሣ እና የተቀናጀ ግብርና ልማትን በከፍተኛ ደረጃ በማስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
🟠 በ2018 ዓ.ም በ30,000 የዓሣ ጭጩቶች የተጀመረው ሰው ሠራሽ ሐይቅ የዓሣ ቁጥሩ አሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
🟠 የዓሣ ልማቱን ወደ 5,700 ሄክታር በማስፋፋት ትልቅ የዓሣ ማከፋፈያ ማዕከል ለመሆን እየሠራ ነው።
🟠 ቀደም ሲል ምንም ዓይነት ልማት ያልነበረበት ቦታ ወደ ስንዴ፣ ቡና እና ዓሣ ልማት ተቀይሯል።
🟠 በወተት፣ በዶሮ፣ በንብና በእንስሳት ማድለቢያ የ"ሌማት ትሩፋት" ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
የግብርና ሚኒስቴር እና የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች፣ የሥልጠና እና የሙያ ድጋፍ ያደርጋሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X