ሱዳን ከሁለት ዓመታት በኋላ በካርቱም ጥላው የነበረውን የሰዓት እልፊ የእንቅስቃሴ ገደብ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች
ሱዳን ከሁለት ዓመታት በኋላ በካርቱም ጥላው የነበረውን የሰዓት እልፊ የእንቅስቃሴ ገደብ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች
በሱዳን ጦር እና በአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በግንቦት 2016 ዓ.ም ተጥሎ የነበረውን የሁለት ዓመት የሌሊት ሰዓት እላፊ ገደብ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግሥት ማንሳቱን ተከተሎ፣ የዋና ከተማዋ ነዋሪዎች አሁን ላይ ለ24 ሰዓታት መንቀሳቀስ እና መሥራት ይችላሉ ተብሏል።
የሰዓት እልፊ ገደቡ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11:00 ሰዓት የእንቅስቃሴ ገደብ የሚጥል የነበረ ሲሆን፣ የንግድ እንቅስቃሴዎችም እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ እንዲካሄዱ የሚያስገድድ ነበር።
የቀጠሉ የጸጥታ እርምጃዎች፦
🟠 የወታደራዊ ጥበቃ እና የፈተሻ ጣቢያዎች፦ የሕዝብ ተቋማትን፣ ድልድዮችን እና የወንዝ መሻገሪያዎችን ለመጠበቅ የወታደራዊ ጥበቃ ዝውውሮች እና የጸጥታ ፈተሻ ጣቢያዎች በመላ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ ይቆያሉ።
🟠 የመታወቂያ ሰነድ መያዝ ግዴታ መሆኑ፦ በምሽት ሰዓት የሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች በማንኛውም ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ የመታወቂያ ሰነድ እንዲይዙ በጥብቅ ተመክረዋል።
🟠 በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የተጣለ ገደብ፦ ሕጋዊ ቪዛ ወይም የፈቃድ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ካርቱም ግዛት እንዳይገቡ ተከልክለዋል። ይህንን ሕግ የሚጥሱ የትራንስፖርት ኩባንያዎች እና አሽከርካሪዎች ሕጋዊ እርምጃ ይጋፈጣሉ።
ጦርነቱ በሚያዝያ 2023 የተጀመረባት ካርቱም፣ በወርሃ መጋቢት 2025 በሱዳን ጦር ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውላለች። መንግሥትም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከነበረበት ጊዜያዊ አስተዳደራዊ ከተማ ፖርት ሱዳን ወደ ዋና ከተማው ካርቱም ተመልሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X