ኢትዮጵያ የጤና ተቋማትን የዲጂታል መረጃ በአንድ ቋት የሚያሰባስብ የአሠራር ማዕቀፍ ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የጤና ተቋማትን የዲጂታል መረጃ በአንድ ቋት የሚያሰባስብ የአሠራር ማዕቀፍ ይፋ አደረገች

ጤና ሚኒስቴር “የኢትዮጵያ የዲጂታል ጤና ኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር” የተሰኘ የኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የሚጠቀምባቸው የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ አሠራሮች እርስ በእርሳቸው የሚገናኙበትና የሚናበቡበት ሀገራዊ የአሠራር ማዕቀፍ አስተዋውቋል፡፡

የዚህ አሠራር ዋና ዋና ጥቅሞች፡፦

ተቋማትን፣ አሠራሮችን፣ የሰው ኃይልን፣ ቁሳቁሶችን፣ መረጃን እና ቴክኖሎጂን በአንድ የጋራ ሥነ-ምኅዳር ያስተሳስራል፡፡

ታካሚ ከአንድ ሆስፒታል ወደ ሌላ ሆስፒታል ሲዛወር የሕክምና ታሪኩ በዲጂታል መንገድ እንዲተላለፍ ያደርጋል።

የታካሚዎች የሕክምና መረጃ ምሥጢራዊነቱ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በአንድ የጋራ ሥርዓት እንዲያዝ ያደርጋል።

ሚኒስቴሩ ትክክለኛ እና ፈጣን የጤና መረጃ በማግኘት የተሻለ የፖሊሲና የአመራር ውሳኔ እንዲሰጥ ይረዳዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0