ሩሲያ በቅርቡ በማሊ ከተፈጸሙት የታጣቂዎች ጥቃቶች ጀርባ የፈረንሳይ እና ዩክሬን እጅ አለበት ብላ ትጠረጥራለች - ዲፕሎማት

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በቅርቡ በማሊ ከተፈጸሙት የታጣቂዎች ጥቃቶች ጀርባ የፈረንሳይ እና ዩክሬን እጅ አለበት ብላ ትጠረጥራለች - ዲፕሎማት

​ ሞስኮ በቅርቡ ማሊ ውስጥ ከተፈጸሙት መጠነ-ሰፊ የታጣቂዎች ጥቃቶች ጀርባ የፈረንሳይ እና የዩክሬን ልዩ ኃይሎች አሉ ብላ ለማመን የሚያስችል "በቂ መሠረት" እንዳላት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን አርቲዮም ስቱዴኒኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ዲፕሎማቱ በሳኅል ቀጣና ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን ፈረንሳይ አሁን ሥልጣን ላይ ያሉት መንግሥታትን በመገልበጥ ለፓሪስ ታማኝ የሆኑ አገዛዞችን ለማስቀመጥ ሆን ብላ ቀጣናውን እያተራመሰች እንደምትገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ ብለዋል።

​ ታህሳስ 3 ቀን በቡርኪና ፋሶ ተሞክሮ በነበረው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የፈረንሳይ እጅ እንዳለበት የሚያመለክተውን የሩሲያ የስለላ ተቋም መግለጫ ያስታወሱት ዲፕሎማቱ፤ በወቅቱ ዓማፅያኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬን ለማስወገድ ሞክረው እንደነበር ገልጸዋል።

በቅርቡ በማሊ የተሞከሩት የታጣቂዎች ጥቃቶች "በሩሲያ ጦር የአፍሪካ ኮር ጀግንነት ሊከሽፉ ችለዋል" ሲሉ ስቱዴኒኮቭ ተናግረዋል።

​🟠 በሚያዝያ ወር በማሊ በከሸፉት ጥቃቶች ታጣቂዎቹ ከ2,500 በላይ አባሎቻቸውን እና 102 ተሽከርካሪዎችን እንዳጡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በወቅቱ ገልጾ ነበር።

​🟠 ታጣቂዎቹ በዩክሬን እና በአውሮፓውያን ቅጥረኛ አሠልጣኞች ድጋፍ ሲሠለጥኑ የቆዩ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0