ሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት የዶላር ጥገኝነት በኋላ ብሔራዊ ገንዘቧን ልትመልስ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት የዶላር ጥገኝነት በኋላ ብሔራዊ ገንዘቧን ልትመልስ ነው
ሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት የዶላር ጥገኝነት በኋላ ብሔራዊ ገንዘቧን ልትመልስ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.08.2026
ሰብስክራይብ

ሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት የዶላር ጥገኝነት በኋላ ብሔራዊ ገንዘቧን ልትመልስ ነው

ሶማሊያ አዲስ የሀገር ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን ሳታትም ከቆየች 35 ዓመታት በኋላ የሶማሊያ ሺሊንግን ዳግም ለመመለስ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።

የማዕከላዊ ባንኩ ዝግጅቱ በላቀ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፦

▪ የታቀደውን የገንዘብ ቦርድ ሥርዓት አደረጃጀት የሚመለከቱ ማሻሻያዎች ፓርላማው እየገመገመ ነው፣

▪ ባንኩ የውጭ ምንዛሬ እና የተጠባባቂ ገንዘብ አስተዳደር ደንቦችን እያጠናቀቀ ነው።

ይህ ማሻሻያ ለምን አስቸኳይ ሆነ?

የገንዘብ ሥርዓቱን ማሻሻያ ለማፋጠን በርካታ ምክንያቶች ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ፦

▪ ያረጁ የሺሊንግ ኖቶች በንግድ ተቋማት ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነት ማጣታቸው፣

▪ ሶማሊያ የገጠማት የዓለም አቀፍ ድጋፍ ቅነሳ፣

የአል-ሸባብ* የደህንነት ስጋቶች የመንግሥት ተቋማትን ማዳከሙ።

እነዚህ ተደራራቢ ተግዳሮቶች በብሔራዊ ገንዘቡ ላይ ያለውን የሕዝብ እምነት ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት አፋጥነውታል።

በርካታ አስርት ዓመታትን ያለ ብሔራዊ ገንዘብ ያሳለፈችው ሶማሊያ፦

የሶማሊያ የገንዘብ ሥርዓት እ.ኤ.አ በ1991 የዚያድ ባሬ መንግሥት መውደቁን ተከተሎ በተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ ወድቋል።

ይህም መጠነ ሰፊ ተፅዕኖ ነበረው፦

▪ ማዕከላዊ ባንኩ ገንዘብ የማተምና የማስተዳደር አቅሙን አጥቷል፣

▪ ገበያው በፎርጅድ የገንዘብ ኖቶች ተጥለቅልቋል፣

▪ የአሜሪካ ዶላር የሕዝቡ የዕለት ተዕለት ንግድ፣ ቁጠባ እና የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክ ክፍያዎችን ቀስ በቀስ ተቆጣጥሮታል።

* በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0