ኢትዮጵያ የግል የኃይል አምራቾች ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ እንዲያቀርቡ ልትፈቅድ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ የግል የኃይል አምራቾች ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ እንዲያቀርቡ ልትፈቅድ ነው
ኢትዮጵያ የግል የኃይል አምራቾች ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ እንዲያቀርቡ ልትፈቅድ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.08.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የግል የኃይል አምራቾች ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ እንዲያቀርቡ ልትፈቅድ ነው

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የተሻሻለው ብሔራዊ የኃይል ፖሊሲ፤ የግል ኤሌክትሪክ አምራቾች የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያን በመጠቀም ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ እንዲያቀርቡ የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎችን አካቷል ተብሏል።

 

ይህ የተገለጸው ዓለም ባንክ ይፋ ባደረገው የፕሮግራም ሰነድ ሲሆን እርምጃው በመንግሥትና በግል ዘርፍ አጋርነት በኃይል ማስተላለፍ እና ማከፋፈል ሂደት ውስጥ የግሉ ዘርፍ ለሚኖረው ተሳትፎ መሠረት የሚጥል እንደሆነ ተነግሯል።

ማሻሻያው የግል አምራቾች "ከፍተኛ ኃይል ለሚጠቀሙ የኢንዱስትሪ ተጠቃሚዎች በቀጥታ ማቅረብን ጨምሮ ብሔራዊ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን እንዲያገኙ እና እንዲጠቀሙ" የሚያስችል ነው ሲል የዓለም ባንክ ሪፖርት አብራርቷል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0