76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ
19:15 27.08.2026 (የተሻሻለ: 19:24 27.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ
በጉባኤው ወቅት የጤና ሚኒስትሮች ታሪካዊ የሆነውን የ10 ዓመት የጤና ባለሙያዎች አስተዳደር መርኃ-ግብር በይፋ ማጽደቃቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ላለፉት ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ የተካሄደው ጉባኤ አበይት ትኩረቶች፦
🟠 እያሽቆለቆለ ለመጣው ዓለም አቀፍ የጤና ዘርፍ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ አኅጉራዊ እልባት መፈለግ፣
🟠 ሁለንተናዊ የጤና ተደራሽነትን ማፋጠን፣
🟠 የጤና ሉዓላዊነትን ማጠናከር፣
🟠 የአፍሪካን የጤና ባለሙያዎች ዕድገት ማፋጠን።
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሃመድ ያቁብ በመዝጊያ ንግግራቸው፤ "የአኅጉራችን የጤና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሌላ የትም ቦታ አይፃፍም። ሊፃፍ የሚችለው በአፍሪካውያን፣ በአፍሪካውያን መሪነት፣ በአፍሪካውያን ተቋማት፣ በአፍሪካውያን የፈጠራ ሥራዎች፣ በአፍሪካውያን የላቀ ብቃት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በአፍሪካውያን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X