በኡጋንዳ የተከሰተው የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ
17:39 27.08.2026 (የተሻሻለ: 17:44 27.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኡጋንዳ የተከሰተው የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ
የዓለም ጤና ድርጅት ምንም ዓይነት የቫይረሱ ስርጭት አለመኖሩን በዚህ ሳምንት ባደረገው ክትትል ካረጋገጠ በኋላ በኡጋንዳ ተከስቶ የነበረው የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን ገልጿል።
የቡንዲቡግዮ ቫይረስ በፍጥነት ቢሰራጭም ምንም ዓይነት መለወጥ አለማሳየቱን፤ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ዳይሬክተር ዶክተር ማሪ ሮዝሊን ቤሊዛየር ገልጸዋል።
ኡጋንዳ 20 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እና የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ካስመዘገበች በኋላ ከኢቦላ ነፃ መሆኗ በይፋ የታወጀው ሐምሌ 21 ቀን ነበር።
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወረርሽኙ ተባብሷል
በሌላ በኩል የተጠረጠሩ ሰዎችን የመከታተልና የመመርመር ሥራ ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም፤ በኮንጎ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ መሄዱን ዶክተር ቤሊዛየር ተናግረዋል።
የኮንጎ ባለሥልጣናት ከ5 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እና የ2 ሺህ 700 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹ ሲሆን ይህም በሀገሪቱ የተከሰተውን ወረርሽኝ በታሪክ ሁለተኛው ገዳይ የኢቦላ ወረርሽኝ አድርጎታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X