አዲስ አበባ በአዳዲስ እና ዘመናዊ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች ልማቷን አስቀጠለች

ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ በአዳዲስ እና ዘመናዊ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች ልማቷን አስቀጠለች

 

በጎተራ፣ በቦሌ፣ በየካ እና በቀበና አካባቢዎች የተገነቡ አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎች እና የገበያ ማዕከላት በ​ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትናንት ተመርቀዋል።

 

ፕሮጀክቶቹ በመዲና ያለውን የትራንስፕርት እንቅስቃሴ የሚያሻሽሉ እና የትራፊክ መጨናነቅን የሚቀርፉ ናቸው ተብሏል፡፡

በማዕከላቱ ከተካተቱ መገልገያዎች ውስጥ፦

▪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀሮች፣

▪ ሰፋፊ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣

▪ የንግድ ሱቆች፣ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች፣ የሕፃናት መጫወቻና የማረፊያ ቦታዎች።

“ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም…በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል” ሲሉ ከንቲባ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0