ሞስኮ የሩሲያ እና አፍሪካን ጠንካራ ቁርኝት በማጉላት የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ ቀንን አከበረች

ሰብስክራይብ

ሞስኮ የሩሲያ እና አፍሪካን ጠንካራ ቁርኝት በማጉላት የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ ቀንን አከበረች

የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ (ሳድክ) ቀን በደቡብ አፍሪካ ክልል ሰላም፣ ደህንነት እና ዘላቂ ልማትን በማስፋፋት ረገድ ለኀብረቱ የለውጥ ሚና እውቅና ለመስጠት በየዓመቱ ነሐሴ ወር ይከበራል።

በሞስኮ የውጭ ሀገራት ሥነ-ጽሑፍ ቤተ-መጻሕፍት በተካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፤ ከደቡባዊ አፍሪካ ክልል የመጡ ተማሪዎች ያቀረቡትን የሙዚቃ ኮንሰርት እና የሳድክ አባል ሀገራትን ማራኪ የባሕል ቅርሶች ኤግዚቢሽን ያካተተ ነበር።

በሩሲያ የዛምቢያ ኤምባሲ የአስተዳደር ባልደረባ አንጌሳ ቻላ፤ በሩሲያ እና ሳድክ መካከል ያለው የኢኮኖሚ እና የባሕል አጋርነት የማደግ አቅም "በጣም ከፍተኛ" መሆኑን በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

 

በሩሲያ የዛምቢያ ኤምባሲ ጊዜያዊ የተልዕኮዎች ኃላፊ አርክሪቲየስ ምዋካያያ በበኩላቸው፤ "ትርጉም ያለው የኢኮኖሚ አጋርነት እንዲኖረን አፍሪካ ትኩረት ልታደርግባቸው ከሚገቡ ሀገራት መካከል ሩሲያ አንዷ ናት። በጊዜ ሂደት ሩሲያ እና አፍሪካ ዕድሎቻቸውን በአግባቡ ከተጠቀሙ በጣም ጠንካራ የሆነ አጋርነት ይኖረናል" ብለዋል።

የበዓሉን ደማቅ ሁኔታ በቅርበት ለመታዘብ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ያዘጋጀውን ቪዲዮ ይመልከቱ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0